Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በነገው የለንደን ማራቶን ላይ ይወዳደራሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለማችን ታዋቂ አትሌቶች የሚሳተፉበት የ2024 የለንደን ማራቶን በነገው ዕለት ይካሄዳል፡፡

በውድድሩ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን÷ በወንዶች አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ ሞስነት ገረመውና ታምራት ቶላ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸዋል።

በሴቶች ደግሞ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው፣ ትዕግስት አሰፋና አልማዝ አያና ውድድሩን በአሸናፊነት ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ውድድሩን በአንደኝነት የሚያጠናቅቁ የ55 ሺህ ዶላር፣ ሁለተኛ የሚወጡት የ30 ሺህ ዶላር ሶስተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁት ደግሞ የ22 ሺህ 500 ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡

ውድድሩ ከጥዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.