Fana: At a Speed of Life!

ክልከላ ተጥሎባቸው ከነበሩ ተሽከርካሪዎች መካከል 68ቱ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓጓዙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ ወደብ ተከማችተው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ክልከላ ተጥሎባቸው ከነበሩ ተሽከርካሪዎች መካከል 68 መኪናዎች ወደ ሀገር ቤት እየተጓጓዙ ነው።

ተሽከርካሪዎቹ ውሳኔ እስኪያገኙ ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲቆዩ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ነው ወደ ሀገር ቤት እየተጓጓዙ ያለው።

በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) መረጃ እንዳመለከተው፤ ተሽከርካሪዎቹ በኢባትሎ የየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ነው ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዙ ይገኛሉ።

የገንዘብ ሚኒስቴር መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥር ቀ/ሃ/7/14/525 ባስተላለፈው መመሪያ በውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ ምክንያት ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በፊት የባንክ ፈቃድ የተሰጠባቸው ወይም ያለ ውጭ ምንዛሬ ፈቃድ የተገዙ እና ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ያልቻሉ በጅቡቲ ወደብ ላይ ተከማችተው የሚገኙ ተሽከርካሪዎች በኢባትሎ በኩል ተጓጉዘው ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡና በድሬደዋ ወደብና ተርሚናል ቆይተው ውሳኔ እንዲጠባበቁ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.