Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በውድድሩ ከ10 ሺህ በላይ ግለሰቦች እንዲሁም ከ22 ክለቦች የተወጣጡ አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተመርተው ለዓለም አቀፍ ክለቦች የሚቀርቡ የስፖርት ትጥቆችን ማስተዋወቅ የሩጫው ዓላማ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

መርሐ ግብሩ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የውጭ ምንዛሬ ወጪን በማዳን ውጤት እያስገኘ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ያዘጋጁት ውድድሩ መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በውድድሩ በወንዶች ምድብ አትሌት ገመቹ ዲዳ በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ÷ በሴቶች ደግሞ ጌጤ አለማየሁ አሸንፋለች፡፡

በታሪኩ ወ/ሰንበት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.