Fana: At a Speed of Life!

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚገመት ተኪ ምርት ተመረተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚገመት ተኪ ምርት ማምረት መቻሉን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አክሊሉ ታደሰ እንዳሉት÷ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ተኪ ምርት በማምረት፣ የውጪ ምንዛሬ በማስገኘትና ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው።

ባለፉት 9 ወራት ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በተደረገ ጥረት ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚገመት ተኪ ምርት ማምረት መቻሉን ተናግረዋል።

እንዲሁም በ13 ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ተመርተው ወደ ውጪ ከተላኩ የተለያዩ ምርቶች ከ90 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ጠቅሰዋል።

ኢንዱስትሪያል ፓርኮች በዓለም ተወዳዳሪና ጥራት ያለው ምርት እያመረቱ በማቅረብ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን እያገዙ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.