Fana: At a Speed of Life!

ልማት ባንክ ስታርት አፖችን በፋይናንስ ለመደገፍ እየሠራሁ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተጀመሩ ስታርት አፖችን በፋይናንስ ለመደገፍ የሚያስችሉ አሠራሮች ተዘርግተው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታወቀ።

በመንግሥት ልዩ ትኩረት በስፋት የተጀመሩ ስታርት አፖችን በፋይናንስ ለመደገፍ እየሠሩ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ባንኩ ስታርት አፖችን በፋይናንስ ለመደገፍ የሚያስችሉ አሠራሮችን በመዘርጋት ወደ ሥራ መግባቱንም ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀገራዊ የስታርት አፕ ፖሊሲ ይፋ ከመደረጉ ቀደም ብሎ የሌሎች ሀገራትን ልምዶችና አሠራሮች ሲያጠና መቆየቱንም አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባትም ባንኩ የራሱን የአሠራር ሥርዓት ዘርግቶ አሁን ላይ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.