Fana: At a Speed of Life!

አርሶ አደሩ የግብርና ግብዓት በቅርበት እንዲያገኝ እየተሠራ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አርሶ አደሩ የግብርና ግብዓት በአቅራቢያው እንዲያገኝ ቅርንጫፍ ማዕከላትን እያስፋፋሁ ነው አለ፡፡

ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ ግብዓቶችን አርሶ አደሩ በአቅራቢያው እንዲያገኝ ቅርንጫፍ ማዕከላትን ለማጠናከር ትኩረት መሰጠቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክፍሌ ወልደማርያም ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም ኮርፖሬሽኑ ያሉትን 25 ቅርንጫፍ ማዕከላት የተሟላ ፓኬጅና አገልግሎት እንዲይዙ እያደረገ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በተለይም ያሉትን የግብርና ዕምቅ አቅሞች ለመጠቀም የተቀናጀ የግብርና ግብዓት ሜካናይዜሽን ማዕከላትን የማስፋፋት ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ከ500 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የቦንጋ ቅርንጫፍ ማዕከል እየተገነባ መሆኑን ገልጸው÷ በያዝነው ዓመት ግንባታው ተጠናቅቆ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

ማዕከሉ ሲጠናቀቅም በኦሮሚያ ክልል ለጅማ ዞን፣ ጋምቤላ እና ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች የተሟላ አገልግሎት እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.