Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የሰሜን ጎንደር ዞን አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሠዓት ጀምሮ በፓርኩ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ቢምረው ካሳ ተናግረዋል፡፡

በሰው ኃይል የሚቻለውን ለመቆጣጠር ጥረት መደረጉን አንስተው ሰው በማይደርስባቸው ገደላማ አካባቢዎች ያለውን ግን ለመቆጣጠር አለመቻሉን ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡

የአስጎብኚ ማኅበራት፣ የፓርኩ ሠራተኞች፣ የዞን እና የወረዳዎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎችም ቃጠሎውን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

ሁሉም የአካባቢው የኅብረተሰብ ክፍልም በንቅናቄ በመውጣት ርብርብ እንዲያደርግ አሳስበው÷ የክልል እና የፌዴራል ተቋማትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.