Fana: At a Speed of Life!

6ኛው የአፍሪካ ሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት ቀናት የሚቆየውና የአፍሪካ መሪዎች፣ ተወካዮች እና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ሥድስተኛው የአፍሪካ ሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማሻሻልና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኗ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሊወሰድ የሚችል ምሳሌ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ለውጥ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅታ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ፣ እራስን መቻል እና የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት ላይ ያተኮሩ ውጥኖችን መጀመሯንም አስረድተዋል፡፡

እነዚህ ውጥኖች የአርሶ አደሩን የአፈር ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር እና ቴክኖሎጂ ተደራሽነት ማሻሻል እንደሚያካትቱም አስገንዝበዋል፡፡

በቅርቡም የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ፖሊሲዋን በማሻሻል ፈጠራን ለማጎልበት እና የታዳጊ ቴክኖሎጂዎችን አቅም ለመጠቀም ኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት መስጠቷን አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.