Fana: At a Speed of Life!

ፖፕ ፍራንሲስ በዩክሬን¬-ሩሲያና በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ያለው ጦርነት እንዲቆም በድጋሚ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ በዩክሬ-ሩሲያ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በማውገዝ የእርቀ ሰላም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጳጳሱ በቫቲካን ከተማ በሚገኘው በሴንት ፒተር አደባባይ ለተሰበሰቡ ታዳሚዎች አሁንም ቢሆን በሀገራቱ በኩል ሰላም እንዲወርድ ደግሜ ጥሪየን አቀርባለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አክለውም፥ “ለፍልስጤም እና ለእስራኤል ሰላም በየቀኑ እጸልያለሁ እናም የሁለቱ ህዝቦች ስቃይ በቅርቡ እንዲያቆም እና በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ ችግር የደረሰባትን ዩክሬን አንዘንጋት” ብለዋል፡፡

ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ እስራኤል 1 ሺህ 200 ዜጎቿ መገደላቸውና 250 የሚሆኑት መታገታቸውን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት ውጥረቱ እየባሰ መጥቷል።

ይህን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ከባድ የሚባል ውድመት ያስከተለ እና ከ33 ሺህ 900 በላይ ሰዎችን ህይወት ያሳጣ እንደሆነ የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.