Fana: At a Speed of Life!

ለ50 ሺህ መምህራንና የትምህርት አመራር የብቃት ስልጠና ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ክረምት ለ50 ሺህ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የብቃት ስልጠና እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል ።

ስልጠናው የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍና የመምህራን ብቃትን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን÷ በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ይሰጣል ነው የተባለው።

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የትምህርት አመራር መሪ ስራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ(ዶ/ር) መምህራኑ የሚሰለጥኑት በሚያስተምሩት ትምህርትና በማስተማሪያ ዘዴዎች መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል ።

ለ42 ሺህ መምህራን 120 ሰዓት፤ ለ8 ሺህ የትምህርት አመራሮች ደግሞ የ60 ሰዓት ስልጠና እንደሚሰጣቸው የተገለፀ ሲሆን ÷ሲያጠናቅቁም ፈተና እንደሚወስዱ ነው ስራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡

ስልጠናው በመምህራንና የትምህርት አመራሩ ላይ ያለውን የማስተማር ዘዴዎችና የእውቀት ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡

በአልማዝ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.