Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ጥብቅ የትራፊክ ቁጥጥር የሚደረግባቸው 1 ሺህ 12 ቦታዎች ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጥብቅ የትራፊክ ቁጥጥር የሚደረግባቸው 1 ሺህ 12 ቦታዎች መለየታቸው የክልሉ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ገለጸ።

የኤጀንሲው የትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዳይሬክተር አቶ አለሙ ለማ በክልሉ እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቆጣጠር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በክልሉ የተለዩት ቦታዎች በራዳር ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግባቸውና ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።

በክልሉ ባለፉት 9 ወራት ብቻ ከ 800 በላይ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ከ78 በመቶ በላይ የሚሆኑት አደጋዎችም ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር የተፈጠሩ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.