Fana: At a Speed of Life!

በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ 6 ሜዳሊያ በመሰብሰብ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ ሶስት ብርና ሶስት የነሐስ በአጠቃላይ ስድስት ሜዳልያ በማግኘት ውድድሩን አጠናቃለች።

በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ በሱራፌል አላዩ፣ ሚሊዮን ጨፎ እና ቤተል ወልዱ የነሃስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

ቤተልሄም ገዛህኝ፣ ሮማን አሰፋ እና ተመስገን ምትኩ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ቦክስ ለልዑካን ቡድን ሚያዝያ 15 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደርስ ሲሆን ለቡድኑ ደማቅ አቀባበል የሚደረግ መሆኑን ከባህልና ስፖርት ሚስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሰነድ አልባና ከዜግነት አገልግሎት ጋር ያሉ ስራዎች ከሀገር ደህንነት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ በመሆኑ በጥንቃቄና በህግ አግባብ ብቻ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ልዑኩ ባደረገው ጉብኝት የዱባይ ሚሲዮን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ የሚከተለው አሰራር እንደተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባ መሆኑን እንደተመለከተ ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.