አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሪሾን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ ኢነርጂ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በቀጣይ የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በቅርበት ለመስራት መስማማታቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡