Fana: At a Speed of Life!

በወታደራዊ ሳይንስ የተካነ ተተኪ የሠራዊት አመራር የማፍራቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን የሚያስቀጥል እና በወታደራዊ ሳይንስ የተካነ ተተኪ የሠራዊት አመራር የማፍራቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የአመራር ትምህርት ቤት ተገኝተው በስልጠና ላይ ለሚገኙ የዕዙ የበታች ሹሞች የሕይወት ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።

ኢታማዦር ሹሙ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ የሚገኙ የበታች ሹሞች ነገ ላይ የዛሬዎችን ከፍተኛ አመራሮች በመተካት መከላከያን የሚመሩ ናቸው፡፡

በየደረጃው በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የተካነ የነገይቷ ኢትዮጵያ ሠራዊት አመራሮችን የመገንባቱ ሥራ ለነገ የሚባል አይደለም ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ÷ የሰራዊት አመራሮችን  የማሰልጠኑ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ሠልጣኝ የበታች ሹሞች የሠራዊቱ ቁልፍ መሪዎች ለመሆን በርትተው መስራት እንዳለባቸው  ጠቁመው÷በተፅዕኖዎች ሳይበገሩ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌ/ጄ ሹማ አብደታ በበኩላቸው ÷የጠንካራ ሠራዊት መሠረቱ ለሀገሩ የማይደርቅ ፍቅር ያለው ጠንካራ አመራር እንደሆነ አውስተዋል፡፡

ከዚህ አኳያ የዕዙ ማሠልጠኛ የክፍሉን የማድረግ አቅም ለማሳደግ ራሡ በቅቶ ሠራዊቱን የሚያበቃ አመራር የመገንባት ስራን በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ መግለጻቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.