Fana: At a Speed of Life!

በማሌዥያ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ተጋጭተው የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሌዥያ በበረራ ላይ የነበሩ ሁለት የሮያል ባሕር ኃይል ንብረት የሆኑ የጦር ሄሊኮፕተሮች ተጋጭተው የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ፡፡

በአደጋውም ሦስት ሴት የባሕር ኃይል መኮንኖችን ጨምሮ የ10 የሰዎች ሕይወት ማለፉን የሀገሪቱ ብዙኃን መገናኛዎች ዘግበዋል።

ከአንደኛው ሄሊኮፕተር ሰባት ከሌላኛው ደግሞ ሦስት ሰዎች መሞታቸውንም አናዶሉ ዘግቧል፡፡

የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን ዘገባው አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.