Fana: At a Speed of Life!

ከካዳስተር አገልግሎት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከካዳስተር አገልግሎት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ገለጸ፡፡

በኤጀንሲው የይዞታ ምዝገባ መረጃና አገልግሎት ዳይሬክተር ሐሰን ሙሳ እንዳሉት÷ ገቢው የተገኘው ኤጀንሲው በ10 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹ በሰጠው ከ20 በላይ አገልግሎቶች ነው፡፡

96 ሺህ 146 ተገልጋዮችን በማስተናገድ 4 ቢሊየን 524 ሚሊየን 923 ሺህ 369 ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ÷ 88 ሺህ 825 ተገልጋዮችን በማስተናገድ 4 ቢሊየን 177 ሚሊየን 779 ሺህ 123 ብር ተገኝቷል ብለዋል፡፡

ከአገልግሎት ከተሰበሰበው ውስጥም 115 ሚሊየን 337 ሺህ 232 ብሩ ከዋስትና ፈንድ መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.