Fana: At a Speed of Life!

በስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ እየተሳተፉ ያሉ ስታርት አፖች የመወዳደሪያ ስራዎቻቸውን አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፉ ያሉ ስታርት አፖች የመወዳደሪያ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

በመጪው ቅዳሜ በሚጠናቀቀው የስታርት አፖች ውድድር ላይ የሚቀርቡ 20 ስታርት አፖች ናቸው ስራዎቻቸውን ያቀረቡት፡፡

ለውድድር የቀረቡት የስታርርት አፕ ስራዎች በተለያየ መንገድ የማህበረሰብን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ መሆናቸውን ተወዳዳሪዎች አንስተዋል።

በውድድሩ ያለፉ ተወዳዳሪዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ውጤታቸውን እንዲያውቁ ይደረጋልም ተብሏል።

እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ የኢትዮጵያ “ስታርት አፕ” ዐውደ -ርዕይ በሣይንስ ሙዝየም ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉ ይታወሳል፡፡

የዐውደ-ርዕዩ ዓላማ ስታርት አፖች ያላቸውን ምርት፣ አገልግሎትና ፈጠራ ተቋማት፣ የሥራ ኃላፊዎችና ተማሪዎች እንዲጎበኙት ከማስቻል ባለፈ በባለሃብቶችና ስታርት አፖች መካከል ትስስር እንዲፈጠር ማድረግ ነው ተብሏል፡፡

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.