Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያና ዩክሬን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው ድርድር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ዩክሬን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው ድርድር ማካሄዳቸው ተሰማ፡፡

ጦርነት ውስጥ የገቡት ሀገራቱ ፊት ለፊት በመገናኘት ድርድር ያደረጉት በኳታር አሸማጋይነት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በፊት ለፊት ድርድሩም በጦርነቱ ምክንያት በየሀገራቱ ቁጥጥር ሥር ያሉ ህፃናትን ለመለዋወጥ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የሩሲያ የህፃናት እንባ ጠባቂ ማሪያ ልቮቫ ቢሎቫ ተናግረዋል፡፡

በዶሃ ከተካሄደው ድርድር በኋላ 29 ዩክሬናውያን ህፃናት እና 19 ሩሲያውያን ህፃናት ወደ ሀገራቸው እንደሚላኩ ስምምነት ላይ መደረሱን እንባ ጠባቂዋ ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.