Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 4ኛው ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በብቃት ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረገች ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 4ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በብቃት ለማስተናገድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ገለፁ።

አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከተመድ ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሀመድ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ፤ ኢትዮጵያ (ተመድ) ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በብቃት ለማስተናገድ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በውይይታቸውም፤ በኢትዮጵያ እና በተመድ መካከል ስላለው ዘርፈ-ብዙ አጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም በዘላቂ የልማት ግቦች የትግበራ ሁኔታ፣ በመጪው የተመድ የመሪዎች ጉባኤ እና በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይም ምክክር አድርገዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.