Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ በለጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ አህጉር በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች ቁጥር 209 ሺህ 380 መድረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ7 ሚሊየን 360 ሺህ መብለጡን የሚያሳየው የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፤ ከእነዚህም ውስጥ 209 ሺህ 380 ያህሉ በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ናቸው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ416 ሺህ ሲበልጥ፤ በአፍሪካም በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ5 ሺህ 600 ተሻግሯል።

በአፍርካ ከ95 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከወረርሽኙ ማገገማቸውንም የዩኒቨርሲቲው መረጃ የሚያመላክት ሲሆን፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ3 ሚሊየን 454 ሺህ በላይ ሰዎች አገግመዋል።

በደቡብ አፍሪካ 55 ሺህ 421 ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፥ በሀገሪቱ በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ውስጥ 1 ሺህ 206 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 31 ሺህ 505 ሰዎች ማገገማቸውም ነው የተገለፀው።

ግብፅበ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት 38 ሺህ 284 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ ከእነዚህም 10 ሺህ 289 ሰዎች ሲያገግሙ፤ 1 ሺህ 342 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመጣ ኬንያ 3 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ያስታወቀች ሲሆን፥ ከእነዚህም 1 ሺህ 48 ሰዎች ሲያገግሙ፤ 89 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

በጂቡቲ4 ሺህ 373 ሰዎች፣ በኤርትራ 41 ሰዎች፣ በሶማሊያ 2 ሺህ 482 ሰዎች፣ ሱዳን 6 ሺህ 582 ሰዎች እንዲሁም ደቡብ ሱዳን 1 ሺህ 604 በቫይረሱ መያዛቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በኢትዮጵያም እስከ ትናንትናው እለት ባለው መረጃ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 506 የደረሰ ሲሆን፥ ከእነዚህም 401 ሲያገግሙ፤ 35 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.