Fana: At a Speed of Life!

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አመራሮች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ ህብረተሰቡን የማንቃት ስራ አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አመራሮች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ህብረተሰቡን የማንቃት ስራ አከናወኑ።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ ሙለታ በአዲስ አበባ በተዘዋወሩባቸው አካባቢዎች ላይ የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ እና እያደረገ ያለው ጥንቃቄ ደረጃ አሳሳቢ መሆኑን አንስተዋል።

ግንዛቤ የመፍጠሩ ስራ አሁንም ገና አንደሚቀረው መታዘባቸውንም ነው ያመለከቱት።

ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀቱን እና የግል ንፅህናውን በመጠበቁ ረገድ የሚያደርገው ጥንቃቄ አነስተኛ በመሆኑ ዋጋ ያስከፍላል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ የመገናኛ ብዙሃን ግንዛቤ በመፍጠሩ ረገድ ሰፊ ስራ ይጠበቅበናል ብለዋል።

የሚመለከታቸው አካላት ታች ህብረተሰቡ ጋ የሚታየውን ክፍተት ለማስተካከል እንዲሰሩም ነው ያሳሰቡት።

በተመሳሳይ በትናንትናው እለት በጅማ፣ ጎንደር፣ ወላይታ ሶዶ እና ደብረብርሃን የሚገኙ የፋና ኤፍ ኤም ጣቢያዎች አመራሮችም በተመሳሳይ በየከተሞቻቸው በመዘዋወር ግንዛቤ የመፍጠር ቅስቀሳን አካሂደዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.