Fana: At a Speed of Life!

በጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤሊያስ የተጻፈው ‘ሉዱንዳ’ መፅሐፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤሊያስ የተጻፈው ‘ሉዱንዳ’ መፅሐፍ ዛሬ ተመረቀ።

መፅሐፉ አስገራሚ እውነታዎች፣ አስደማሚ ክስተቶች፣ ጠቃሚ መረጃዎችና ሌሎችም የተካተቱበት እንደሆነ ተገልጿል።

ሉዱንዳ ቃሉ ከሀድይሳ ቋንቋ የተወሰደ እንደሆነም የተገለጸ ሲሆን፥ ትርጉሙም ከሁሉም ጫፍ፣ ቅንጭብጭብ፣ ከዚህም ከዚያምማለት እንደሆነም ነው የተጠቆመው፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩ ፀሃፌ ተውኔትና ባለቅኔ አያልነህ ሙላቱ፣ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠን ጨምሮ አንጋፋ ጋዜጠኞች፣ ደራሲያንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ፀሃፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ በዚህ ወቅት፥ ሥነጽሁፍና ጋዜጠኝነት የማይነጣጠሉ እንደሆኑ ጠቅሰው ወጣት ጸሃፊያን መበረታታት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡

ጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤሊያስ በበኩሉ፥ ሉዱንዳ በያዛቸው አስገራሚ እውነታዎች፣ አስደማሚ ክስተቶች፣ ጠቃሚ መረጃዎችን በማካተት ለጠቅላላ ዕውቀት ምንጭነትና ለማጣቀሻነት መገልገል እንደሚቻል ጠቅሷል፡፡

በዚህም መጽሃፉ ዓለም አቀፋዊ ይዘቶችን ያያዙ ድንቃድንቅ፣ ስፖርታዊ፣ ጂኦግራፊያዊ፣ አህጉራዊ፣ ታሪክ፣ ጥበብ፣ ሣይንስና ፈጠራ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ተዳስሰውበታልም ነው የተባለው፡፡

በመሰረት አወቀ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.