Fana: At a Speed of Life!

250 ኢትዮጵያዊን ከኩዌት ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 250 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በዛሬው እለት ከኩዌት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
 
ኢትዮጵያውያኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከውጭ ጉዳይ እና ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
 
ባሳለፍነው ማክሰኞ ሰኔ 2 2012 ዓ.ም 259 ኢትዮጵያውያን ከኩዌት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በያዝነው ሳምንት ከኩዌት እንደሚመለሱ ይጠበቃል።
 
በዛሬው እለት ከኩዌት የተመለሱት ኢትዮጵያውያኑ በተዘጋጀው የለይቶ ማቆያ ቦታ ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ቤተሰቦቸቸው የሚቀላቀሉ ይሆናል።
 
#FBC
 
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.