Fana: At a Speed of Life!

የአይፎን ስልኮች ዋጋ ቀነሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፕል ኩባንያ ምርት የሆኑት አይፎን ስልኮች ዋጋ ከአውሮፓ በስተቀር በሁሉም የዓለም ሀገራት ገበያዎች ላይ መቀነሱ ተነገረ።

ኩባንያው እንዳስታወቀው፤ የፈረንጆቹ 2024 ከገባ ወዲህ ባሉት የመጀመሪያ ሶስት ወራት የስማርት ስልኮች አጠቃላይ ፍላጎት ከ10 በመቶ በላይ ቀንሷል፡፡

ይንንም ተከትሎም የኩባንያው አጠቃላይ ገቢ የ4 በመቶ ቅናሽ በማሳየት ወደ 90 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ዝቅ ማለቱን አስታውቋል።

የተገኘው ገቢ ከሚጠበቀው አንጻር ዝቅተኛ ቢሆንም የከፋ አለመሆኑን የጠቀሰው ኩባንያው፤ ችግሩ ከኮቪድ ወረርሽኝ መከሰት ጋር በተያያዘ በአቅርቦት መዛባቶች ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ገልጿል፡፡

በቅርቡ ይፋ የሚደረጉ ምርቶችና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ላይ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት ተከትሎ በመጪዎቹ ወራት ሽያጩ እንደሚያድግ ያለውን እምነት ኩባንያው መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.