Fana: At a Speed of Life!

በግድቡ ላይ እየተካሄደ ያለው የሶስትዮሽ ውይይት እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አተገባበር ዙሪያ እያደረጉት ያለው ድርድር ለሶስተኛ ቀን በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
 
ድርድሩ በኢትዮጵያ ሊቀመንበርነት ታዛቢዎች በተገኙበት በግድቡ የመጀመሪያው የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ ነው የተካሄደው።
 
በትናንቱ የውይይት ቀንም በግድቡ የመጀመሪያ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ዙሪያ ኢትዮጵያ ባቀረበችው ሰነድ ላይ መክረዋል።
 
ኢትዮጵያም ሃገራቱ ድርድሩ ሁሉንም ወገን እኩል ተጠቃሚ ወደሚያደርግ ውጤት በሚያደርስ የመተማመን መንፈስ ማካሄድ እንደሚገባ ነው ያሳሰበችው።
 
በተጨማሪም የሶስቱን ሀገራት ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል ውጤት የሚያስገኘው ብቸኛው ድርድርም በቴክኒክ ደረጃ የሚካሄደው መሆኑን ግልፅ አድርጋለች።
 
በውይይትም የድርድሩ ታዛቢዎች የሚኖራቸውን ሚና የሚወስን ሰነድንም አዘጋጅተዋል።
 
በድርድሩ በሃገራቱ መካከል የተዘጋጁ ሰነዶች ልውውጥ እና በሃገራቱ መካከል ባሉ መሠረታዊ ልዩነቶች ላይ በቀጣይ ውይይት እንዲደረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
 
የሶስትዮሽ ድርድሩ በነገው እለት በሱዳን ሊቀ መንበርነት ይቀጥላል ተብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.