Fana: At a Speed of Life!

በሽር አል አሳድ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢማድ ካሚስን ከስልጣን አባረሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶሪያው ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ የሃገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢማድ ካሚስን ከስልጣን አባረሩ።

ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ካሚስ የመባረራቸው ምክንያት ግን አልተገለጸም።

በሃገሪቱ እየከፋ የመጣውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተከትሎ የዋጋ ንረት መከሰቱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

አሁን ላይም የአል አሳድ ደጋፊዎች በሚበዙባት ሱዌይዳ ከተማ የእርሳቸውን አስተዳደር የሚቃወሙና ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።

የበሽር አል አሳድ አስተዳደር ደግሞ በምዕራባውያን የተጣለውን ማዕቀብ ኮንኗል።

አሜሪካ በበኩሏ በዘጠኝ አመቱ የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት የአሳድን አስተዳደር ደግፈዋል ባለቻቸው ግለሰቦች ላይ አዲስ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች።

በሶሪያ የእርስ በርስ ግጭት ሳቢያ ከ380 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይነገራል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.