Fana: At a Speed of Life!

የብሪታንያ ኢኮኖሚ በሚያዚያ ወር በ20 ነጥብ 4 በመቶ አሽቆልቁሏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታንያ ኢኮኖሚ በሚያዚያ ወር በ20 ነጥብ 4 በመቶ ማሽቆልቆሉን የሃገሪቱ ስታቲስቲክስ ቢሮ አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስን ተከትሎ በሃገሪቱ በእንቅስቃሴ ላይ የተጣለው ክልከላ ለማሽቆልቆሉ ምክንያት መሆኑም ተገልጿል።

ያጋጠመው ኢኮኖሚያዊ ውድቀት በወር ውስጥ የተመዘገበው ከፍተኛውና ትልቁ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።

ይህም ሃገሪቱ በፈረንጆቹ ከ2008 እስከ 2009 በአጠቃላይ ካጋጠማት የኢኮኖሚ ውድቀት በሶስት እጥፍ የላቀ ነውም ብሏል ቢሮው በመግለጫው።

በወሩ በሃገሪቱ የተመዘገበው አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት መቀነስ ብሪታንያ አይታው የማታውቀውና ከፍተኛው መሆኑን የስታቲስቲክስ ቢሮው ምክትል ጆናታን አቶው ተናግረዋል።

ሁሉም ዘርፎች በኢኮኖሚ ማሽቆልቆሉ ሳቢያ ተጎድተዋልም ነው ያሉት።

ተሽከርካሪ አምራቾች እና የሪል ስቴት አልሚዎች ግን በተለየ መልኩ ከፍተኛ ተጠቂዎች ናቸውም ብለዋል።

ሚያዚያ ወር የከፋው ነበር ያሉት ተንታኞች የሃገሪቱ መንግስት አሁን ላይ ጥሏቸው የነበሩ ክልከላዎችን ማላላት መጀመሩ መልካም መሆኑን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.