Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በማላዊ የጤና ሚኒስትር ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በማላዊ የጤና ሚኒስትር ሃሲና ዳውድ ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር የጋራ ውይይት አካሄዱ።

የሥራ ሀላፊዎቹ በውይይታቸው በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ በኤችአይቪ፣ በቲቢ እና ሞትን በመቀነስ ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶች እንዲሁም በጤናው ዘርፍ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ መክረዋል፡፡

የጤናውን ዘርፍ የማቀናጀት እና የመምራት መመሪያ ለልኡካን ቡድኑ ገለጻ መደረጉንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ዕቅድ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ እንደሚዘጋጅ እና ለክልል ጤና ቢሮዎች እንዴት እንደሚሰራጭም ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

የማላዊ የጤና ሚኒስትር ሃሲና ዳውድ ÷ በሀገራቸው ለጤና አጠባበቅ ፋይናንስ እና ለአጋሮች የትብብር ፕሮጀክቶች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ልምድን በመጋራታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ልዑኩ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴርንም እንደጎበኘ የተገለጸ ሲሆን ÷ በጉብኝቱ አዲስ የተሻሻለው የጤና ፖሊሲና አቅጣጫዎች እንዲሁም መርሆዎችን በሚመለከት ለቡድኑ ገለጻ ተተደርጓል ተብሏል፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.