Fana: At a Speed of Life!

የአለርጂ መከላከያ መንገዶችና ህክምናው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)አለርጂ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት በተለይም ለምግቦች፣ ለአበባ ብናኞች፣ ለአቧራ፣ለአየር ሁኔታ እና መሰል ነገሮች በሚሰጠው ምላሽ እንደሚፈጠር ይነገራል።

ንጥረ ነገሩ ወይም ለሰውነትዎ የማይስማማ ነገሮች ላይ የበሽታ መከላከል ስርዓትዎ የሚሰጠው ምላሽ በሰውነትዎ ላይ አለርጂን ያስከትላል፡፡

በዚህም እብጠት፣ ማስነጠስ ወይም ሌሎች የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን ፥ እንደግለሰቡ የአለርጂ ዓይነትና ሁኔታም ምላሹ የተለያየ እንደሚሆን ነው የሚገለጸው፡፡

አለርጂ እንዴት ይታከማል?

አለርጂን ጨርሶ ማጥፋት እንደማይቻል ይነገራል፤ ሆኖም መከላከል ግን ይቻላል፤ በብዙ የህክምና ባለሙያዎች የሚመከረው አለርጂ ከሚያስከትሉብዎ ነገሮች መራቅ ለነገ የማይባል መፍትሄ ነው፡፡

ሆኖም ይህን አማራጭ መውሰድ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ከሆኑ የህክምና አማራጮችን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

ይህም ከህክምና ባለሙያ ጋር በመነጋገር የመድኃኒት አማራጭን መጠቀም የሚቻል ሲሆን ÷የህክምና ባለሙያን ሳያማክሩ መድኃኒት መውሰድ ግን አይመከርም፡፡

በተጨማሪም ከሃኪምዎ ጋር በመመካከር አለርጂ በቤት ውስጥ ሊታከም የሚችልበትን መንገድ መፈለግ ሌላው አማራጭ ነው፡፡

ይህን የቤት ውስጥ ህክምና ከማድረግዎ በፊት ግን በቤትዎ ውስጥ የሚያዘጋጁት ንጥረ ነገሮች ሌላ አለርጂ ላለመሆናቸው እርግጠኛ መሆን አለብዎ፡፡
አለርጂ ጉንፋን ከሚመስል ማስነጠስ፣ የቆዳ ችግርና ሌሎች ለከፋ ጉዳት የማያስከትሉ ጉዳቶች ቢኖሩትም ለአንዳንድ ሰዎች ለህይወት አስጊ ሊሆንም ይችላል፡፡

እንደአብነትም የምላስ እና የአፍ እብጠት፣ የልብ ምት መጨመር፣ የመተንፈስ ችግር፣ ራስን መሳትና ሌሎች ከፍ ያሉ ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል፡፡

በዚህም አለርጂው ከፍ ያሉ ጉዳቶችን የሚያስከትልብዎ ከሆነ ምንጊዜም ጥንቃቄ ሊለይዎት አይገባም፡፡

ከዚህ ካለፈም የድንገተኛ ህክምና ዘዴዎችን ከሃኪምዎ ጋር ቢወያዩበት ሲል ኽልዝላይን ይመክራል ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.