Fana: At a Speed of Life!

በርንሌይ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መውረዱ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በርንሌይ ሁለተኛው ወራጅ ክለብ መሆኑ ተረጋግጧል።

ዛሬ በተደረገ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ በርንሌይን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም በርንሌይ በ24 ነጥብ ወደ ሻምፒየን ሺፑ መውረዱን አረጋግጧል።

በሌሎች ጨዋታዎች ኢቨርተን ሼፍልድ ዩናይትድን 1 ለ 0፣ ብሬት ፎርድ በርንማውዝን 2 ለ 1፣ ዌስትሃም ሉተንን 3 ለ1 እንዲሁም ክርስታል ፓላስ ወልቭስን 3 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡

ኒውካስል እና ብራይተን ደግሞ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.