Fana: At a Speed of Life!

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ በውጭ አገር ለሚኖሩ ዜጎች ድጋፍ በሚደረግበት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ድጋፍ በሚደረግበት ዙሪያ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓም ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱን በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ የተመራ ሲሆን፤ በውይይቱ የሰላም ሚኒስትር ደኤታ ፍሬአለም ሽባባው፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ፣ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ጆሃን ቦርግስታም፣ የተ.መ.ድ ኤጀንሲዎች በኢትዮጵያ አስተባባሪ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ እና የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ማውሪን አቼንግ ተሳትፈዋል።

በተ.መ.ድ በወጣው መግለጫ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚኒኬ መሰረት የሰዎች እንቅስቅቃሴ በአሁኑ ስዓት ያለውን የኮሮና ወረርሽኝ ተጋላጭነትን እንደሚጨምር ሁሉም አካላት ግንዛቤ መያዝ እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተነስቷል።

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭት ከቀን ወደ ቀን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ በመሆኑ ዜጎች ባሉበት አገር አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዲቆዩ ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሚሆን ግንዛቤ ተይዟል።

ለዚህም የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ እና ኢትዮጵያም አለም አቀፉን ወረርሽኙን በመቆጣጠር ረገድ ተሳትፎዋ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.