Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ከቻይና በሚገቡ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ቀረጥን በሶስት እጥፍ አሳደገች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከቻይና በሚገቡ የኤሌክትሪክ መኪናዎች፣ በፀሃይ ብርሃን የሚሰሩ ባትሪዎች እንዲሁም ብረቶች ላይ የሚጣለውን ቀረጥ በሶስት እጥፍ መጨመሩን አስታውቋል፡፡

በተለይም በድንበር በሚገቡ የቻይና የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ የሚጣለው ቀረጥ ከነበረበት 25 በመቶ አራት እጥፍ ከፍ እንዲል የተደረገ ሲሆን በባትሪዎች እና ኮምፒውተሮች ላይ የሚጣለው ታሪፍ ደግሞ ከ25 በመቶ በእጥፍ እንዲያድግ መደረጉ ተገልጿል።

ውሳኔው ቻይና በመኪና ንግድ ለምትከተለው ፖሊሲ ምላሽ ለመስጠት እና በአሜሪካ ከመኪና ምርት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የስራ እድሎችን ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ቻይና በበኩሏ በአሜሪካ መንግስት የተላለፈውን ውሳኔ እንድምትቃወም ጠቅሳ፤ ለዚህ ያተገባ የታሪፍ ውሳኔ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች፡፡

በውሳኔው መሰረትም አሜሪካ ከቻይና ከሚገቡ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ተጨማሪ 18 በሊዮን ዶላር የቀረጥ ገንዘብ ልታገኝ እንደምትችል ተጠቁሟል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን በቻይና ላይ ያሳለፉት ከፍተኛ የቀረጥ ጭማሪ በአሜሪካ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የቻይናን ከፍተኛ የመኪና ሽያጭ ከሚቃወሙ አሜሪካውያን ድምፅ ለማግኘት ነው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቀደም ሲል ቻይና ወደ አሜሪካ የምታስገባቸው የኤሌክትሪክ መኪናዎች የአሜሪካን የመኪና ኢንዱስትሪ እየገደለ ነው በሚል ከተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ የሰላ ትችት ሲቀርብባቸው እንደነበርም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.