Fana: At a Speed of Life!

የቦይንግ ኩባንያ በድጋሚ ክስ ሊቀርብበት ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቦይንግ ኩባንያ ካሳ ለመክፈል የገባውን ስምምነት በመጣስ ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋር ከህግ ውጭ ስምምነት ለማደረግ መሞከሩን ተከትሎ ክስ ሊቀርብበት መሆኑን የአሜሪካ ፍትህ ዲፓርትመንት አስታወቀ፡፡

የአሜሪካ የፍትህ ዲፓርትመንት ዐቃቤ ሕጎች በፈረንጆቹ 2018 እና 2019 በደረሰው ሁለት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ህይዎታችውን ካጡ ተጎጂ ቤተሰቦች ጋር ዝግ ስብሰባ ማደረጉ ተገልጿል፡፡

በስብሰባውም ኩባንያው ከህግ ውጭ የተጎጂ ቤተሰቦችን በማግባባት ክሱ እንዲቋርጥለት ለማድረግ መሞከሩን የተጎጂ ቤተሰቦች አስረድተዋል፡፡

በፍትህ ዲፓርትመንት የማታለል ወንጀል ክትትል ክፍል ሃላፊ የሆኑት ግሌን ሌዮን÷ ኩባንያው በአሜሪካ በፈረንጆቹ 2021 የተወሰነውን የፀረ-ማጭበርበር ህግ ተላልልፎ መገኘቱን ገልፀዋል፡፡

በዚህም የአሜሪካ ፍትህ ዲፓርትመንት እስከ ፈረንጆቹ ሐምሌ 7 ቀን 2024 ድረስ በኩባያው ላይ በማጭበርበር ወንጀል ሌላ ክስ እንደሚመሰረትበት አስታውቋል፡፡

ቦይንግ ኩባንያ ቀደም ሲል ከተጎጂ ቤተሰቦች የቀረበበትን ክስ ተከትሎ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ስምምነቱን በማፍረስ ክሱን ለማጭበርበር ሞክሯል መባሉን ኤንቲዲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.