Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ ጦር መሳሪያ ለእስራኤል ልትልክ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ ጦር መሳሪያና ተተኳሽ ለእስራኤል ለመላክ ማቀዱን አስታውቋል።
 
የባይደን አስተዳደር ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ ጦር መሳሪያ ወደ እስራኤል እንደሚልክ ያስታወቀው በራፋህ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
አስተዳደሩ ቁልፍ ለሆኑ የምክር ቤት አባላት ለእስራኤል ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የሆነ የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ እንደሚልክ ማስታወቁን ሦስት የኮንግረስ የእርዳታ ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡
 
አስተዳደሩ በቅርቡ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ አቅርቦትን ካገደ ወዲህ ሌላ የጦር መሳሪያ ወደ እስራኤል ለመላክ ሲያቅድ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
 
ይሁን እንጂ የመሳሪያ ድጋፉ ለእስኤል የሚቀርብበትን ጊዜ በተመለከተ የተባለ ነገር አለመኖሩ ነው የተገለጸው፡፡
 
የባይደን አስተዳደር በደቡዊ ጋዛ በራፋህ ከተማ በሲቪሎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በመስጋት ለእስራኤል ሊያደርግ የነበረውን የጦር መሳሪያ አቅርቦት መግታቱ ይታወሳል፡፡
 
ይሁን እንጂ አሁን ላይ የ700 ሚሊየን ዶላር መድፍ ጥይቶች፣ የ500 ሚሊየን ዶላር የጦር ተሽከርካሪዎች እና የ60 ሚሊየን ዶላር ሞርታሮችን ያካተተ የድጋፍ ማዕቀፉ መፍቀዱን ሒንዱስታን ታይምስ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.