Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሕመድ ሽዴ ከካናዳ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ጋር በሀገራቱ የኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ከካናዳ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር አሕመድ ሁሴን ጋር በሁለቱ ሀገራ የኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ መክረዋል፡፡

አቶ አህመድ ሺዴ በወቅቱ፥ የካናዳ መንግስት ለኢትዮጵያ ልማት በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ደረጃ የሚያደርገውን የቆየና ተከታታይነት ያለው ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሀገሪቱ እየታዩ ያሉ ለውጦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማሳደግ እንደሚገባም ነው አጽንኦት ሰጥተው የገለጹት።

የካናዳ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር አህመድ ሁሴን በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ ያለውን ለውጥ አድንቀው፥ ሀገራቸው በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በተለይም በሴፍቲኔት እና በሠላም ግንባታ ስራዎች ላይ ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ፣ በባለብዙ ወገን እና ቀጣናዊ የልማት ጉዳዮችን ጨምሮ በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.