Fana: At a Speed of Life!

የካርቱም ቀጣናዊ ተልዕኮ ማስፈጸም ማዕከል /ሮክ/ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የካርቱም ቀጣናዊ ተልዕኮ ማስፈጸም ማዕከል /ሮክ/ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርጓል።

በአፍሪካ ሕብረት ሥር የተቋቋመው ሮክ በአዲስ አበባ የመከረው ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ ም/ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ፣ የካርቱም ቀጣናዊ ተልዕኮ ማስፈጸም ማዕከል አባል ሀገራት ተወካዮች እንዲሁም የኢንተርፖል እና ዩሮ ፖል ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሮክ በአፍሪካ ሕብረት ሥር የተቋቋመ ሲሆን÷ በአውሮፓ ሕብረት ድጋፍ እንደሚደረግለትም ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል በትብብር የሚሰሩበት ተቋም መሆኑም ይታወቃል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አባል የሆኑበት ሮክ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከልና ለመዋጋት አይነተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.