Fana: At a Speed of Life!

ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችን ከሐሰተኛ ሰነዶች መለየት በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችን ከሐሰተኛ ሰነዶች መለየት በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ልምድ ለመለዋወጥ እና ድጋፍ ለማድረግ በኢትዮጵያና ቻይና ተቋማት መካከል ስምምነት ተደረገ፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ከቻይና ብሔራዊ የኢሚግሬሽን አስተዳደር ምክትል ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በተለይም የኢሚግሬሽን ዘርፉን ከማዘመን፣ የድንበር ቁጥጥር ስርዓቶችን ማሻሻልን ጨምሮ በአቅም ግንባታ ዙሪያ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችን ከሐሰተኛ ሰነዶች መለየት በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ልምድ ለመለዋወጥ እና ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

ምክትል ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ልዩ ሚና የምትጫወት ሀገር መሆኗን አንስተው÷ ዘርፉን ማዘመንና ማሻሻል በዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ዙሪያ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን ተናግረዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትንም ለልምድ ልውውጥ ወደ ተቋማቸው ጋብዘዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.