Fana: At a Speed of Life!

የህግ ባለሙያ አቶ አምሃ መኮንን የዘንድሮውን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማትን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን የዘንድሮውን የፈረንሳይ ጀርመን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማት አሸንፈዋል።

ጠበቃ አምሃ መኮንን በኢትዮጵያ በነበረው አስቸጋሪ ወቅት እና ጊዜያት ሁሉ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት እና ነጻነት መከበር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ሽልማቱ የተበረከተላቸው።

ሽልማቱን የጀርመንና የፈረንሳይ አምባሳደሮች ያበረከቱት ሲሆን፥ በስነ ስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና የሙያ ባልደረቦቻቸው ተገኝተዋል።

የፈረንሣይ ጀርመን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማት በየዓመቱ በፈረንጆቹ ታህሳስ 10 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በዓለም ዙሪያ ለ15 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሚሰጥ ነው።

አቶ አምሃ መኮንን ይህ ሽልማት በኢትዮጵያ ለነፃነትነ እና ለዴሞክራሲያዊ ትግል ሲታገሉ ለነበሩ እና ዋጋ ለከፈሉ ሁሉ የተሰጠ እውቅና ነው ብለዋል።

አቶ አምሃ መኮንን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አማካሪና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅትና የሰብዓዊ መብቶች ጠበቆች እና በኢትዮጵያ የዲጂታል መብቶች አውታር መረብ መስራች ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.