Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቡሩንዲዉ ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ሀዘቸውን የገለፁት አዲስ አበባ በሚገኘው የቡሩንዲ ኤምባሲ በመገኘት መሆኑን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ፒዬር ንኩሩንዚዛ በ55 ዓመታቸው በድንገተኛ የልብ ህመም ባሳለፍነው ማክሰኞ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል።

በፈረንጆቹ 19 63 የተወለዱት ንኩሩንዚዛ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2005 ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ቡሩንዲን መርተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.