Fana: At a Speed of Life!

ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቼልሲው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡

ፓልመር የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች የመጨረሻ እጩ የነበሩትን ኧርሊንግ ሃላንድ እና ቡካዮ ሳካን በመበልጥ ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡

በ42 ሚሊየን ዩሮ ከማንቼስተር ሲቲ ቼልሲን የተቀላቀለ ሲሆን ፥ በውድድር ዓመቱ ደካማ አቋምን ባሳየው ቼልሲ 22 ጎሎችን በማስቆጠር 10 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡

የ22 ዓመቱ እንግሊዛዊ ቀደም ሲል የቼልሲ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.