Fana: At a Speed of Life!

እንግሊዝ ከአልኮል መጠጥ ጋር በተያያዘ ችግር በዓመት 27 ቢሊየን ፓውንድ ታወጣለች ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እንግሊዝ በመጠጥ ለሚመጣ የጤና እና ማህበራዊ ጉዳት በዓመት 27 ቢሊየን ፓውንድ እንደምታወጣ አዲስ ጥናት አመላከተ።

ችግሩ በብሔራዊ የጤና አገልግሎት፣ በማህበራዊ አገልግሎት፣ በወንጀል የፍትህ ስርዓት እና በገበያ ዋጋ ላይ የ37 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን እንደደረሱበት ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በፈረንጆቹ 2003 የተጠናው ጥናት በጉዳዩ ሊወጣ የሚችለውን ወጪ በ18 ነጥብ 5 ቢሊየን እና በ20 ቢሊየን ፓወንድ መካከል እንደሚሆን ግምቱን ማስቀመጡ ተወስቷል፡፡

በፈረንጆቹ 2022 ሚያዝያ ወር ላይ ይፋ የተደረጉ አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩትም ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ከአልኮል ጋር በተያያዘ ችግር ህይወታቸው አልፏል፡፡

መጠጥ የልብና የደም ሥር ፣ የጉበት፣ ስትሮክ እና የምግብ መፈጨት ችግርን ጨምሮ ከብዙ የጤና ችግሮች ጋር የተያያዙ ከሠባት የካንሰር ዓይነቶችጋር የተገናኘ መሆኑ ይነገራል።

ከዚህም ባለፈ አልኮል በግለሰብ እና በማህበረሰብ ላይ ሰፊ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ ጥናቶችን ጠቅሶ የዘገበው ዘ ጋርዲያን ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.