Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን መርቀው ከፈቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በቢሾፍቱ መርቀን የከፈትነው የመከላከያ ሪፈራል ሆስፒታል እጅግ ዘመናዊ የሆነ የህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጥ ነው ብለዋል።

በዚህም የሞሎኪዩላር ላብራቶሪ፣ የአጥንት ምርመራ ማዕከል፣ ባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ክፍል እና እንደ የኩላሊት እጥበት፣ የነርቭ፣ የሳምባ እና መተንፈሻ አካላት ህክምና አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

በሀገራችን ካሉ ግንባር ቀደም ዘመናዊ ሆስፒታሎች አንዱ በመሆኑም በትውልድ ታላቅ ሀገራዊ ርዕይ ተሰርተው ለዜጎች አገልግሎት የዋሉ ፕሮጀክቶች ማሳያ ሆኗል ሲሉም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.