Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ25ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀድያ ሆሳዕና አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በበረከት ወልዴ ጎል ሲመራ ቢቆይም ከረፍት መልስ ኡመድ ኡኩሪ ባስቆጠራት ጎል ሀድያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋርቷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ፈረሰኞቹ በ40 ነጥብ 4ኛ ደራጃ ሲቀምጡ ሀድያ ሆሳዕና በ38 ነጥቦች 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ የዋንጫ ተፎካካሪው መቻል ከመመራት ተነስቶ ሀዋሳ ከተማን 3 ለ 2 ተሸንፏል፡፡

የሀዋሳ ከተማን ሁለት ጎሎች አሊ ሱሌማን ሲያስቆጥር ለመቻል ከንዓን ማርክነህ(ሁለት) እና አብዱ ሙተለቡ እቆጥረዋል፡፡

በውጤቱ መስረትም መቻል ነጥቡን ወደ 50 ከፍ በማድረግ የዋንጫ ተፎካካሪነቱን ሲያጠናክር ሀዋሳ ከተማ በ33 ነጥቦች በነበረበት 10ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.