Fana: At a Speed of Life!

ልጁን ‘የካንሰር በሽተኛ ነው’ በማለት ሲለምንበት የተገኘ ወላጅና ግብረ-አበሩ ተያዙ 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤናማ ልጁን ‘የካንሰር በሽተኛ ነው’ በማለት ሲለምንበት የተገኘ ወላጅን እና ግብረ-አበሩን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በወንጀሉ የተጠረጠረው ግለሰብ ልጁን የካንስር በሽተኛ በመሆኑ ለማሳከም ከአዋሽ 7 ወደ አዲስ አበባ መምጣቱንና ልጁን ለማሳከም፣ ለምግብ እንዲሁም ማደሪያ መቸገሩን በመግለፅ ከአንድ ግብረ-አበሩ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ሲለምን መቆየቱን ገልጿል።

የህፃኑ አባት አቶ ጃዋር አብዱላሂ እና አህመድ ከሊፋ የተባለው ግብረ-አበሩ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ሰነዓ ሆቴል አካባቢ የማታለል ተግባራቸውን ሲፈፅሙ ፖሊስ በጥርጣሬ ይዟቸዋል።

በዚህም የሀኪም ማስረጃ ሲጠየቁ ምንም አይነት ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል።

ህፃኑ በፖሊስ ጣቢያ  ሲጠየቅ ጤነኛ መሆኑን እና ምንም አይነት ቁስል አንገቱ ላይ እንደሌለበት ማረጋገጡን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የደንበል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል፡፡

የህፃኑ አባትና ግብረ አበሩ በህጻኑ አንገት ላይ ፕላስተር ለጥፈው ሲለምኑ እንደነበር ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል ሲል ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት በልመና ያገኙት ከ1 ሺ 240 ብር በላይ በኤግዚቢትነት ይዞ ፖሊስ ምርመራውን መቀጠሉን አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.