Fana: At a Speed of Life!

ለቀድሞ ተዋጊዎች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራት መለየታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቀድሞ ተዋጊዎች የመመዝገቢያ፣ የመመገቢያ፣ ስልጠና እና የመኝታ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራት መለየታቸውን ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽኑ በማህበራዊ ትስስሩ ገጹ እንዳመለከተው፤ በመቀሌ በምክክር ላይ የነበረው የመልሶ ማቋቋም ባለድርሻ አካላት ቡድን የተመረጡ የምዝገባ ጣቢያዎችን ጎበኝቷል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በመጀመሪያው ዙር ከትግራይ ክልል መልሶ የሚያቋቁማቸውን የቀድሞ ተዋጊዎች ምዝገባ ለማካሄድ፣ የስነ ልቦና ድጋፍና የተሀድሶ ስልጠናዎች ለመስጠት እንዲቻል ከተለዩት አምስት ማዕከላት ውስጥ የአጉላዕና ዕዳጋ ሐሙስ ማዕከላትን ተጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ማዕከላቱ በየዙሩ ለሚገቡ የቀድሞ ተዋጊዎች የመመዝገቢያ፣ የመመገቢያ፣ ስልጠና እና የመኝታ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችና በአጭር ጊዜ መስተካከል የሚገባቸዉ ተግባራት መለየታቸው ታይቷል።

በቀጣይ ሊከናወኑ በሚገባቸዉ ተግባራት ላይም የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን የኮሚሽኑ መረጃ አመልክቷል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በመሩት ቡድን የኮሚሽኑና የክልሉ አመራሮች እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.