Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የቡድኑ አባል የነበሩት ኃ/ማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ1954 ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋች የነበሩት ኃይለማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

በቅፅል ስማቸው “ሻሾ” በሚል በስፖርት ቤተሰቡ በስፋት የሚታወቁት ኃይለማርያም መኮንን÷ ከ1940ዎቹ መጨረሻ እስከ 60ዎቹ መጀመሪያ በነበረው የተጫዋችነት ሕይወታቸው ለጥቅምት 23፣ ሸዋ ፖሊስ፣ ዳኘው እና ሸዋ ምርጥ ተጫውተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንንም በተለያዩ የዕድሜ ዕርከኖች እና ዋናው ቡድን ያገለገሉ ሲሆን÷ በ1954 ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍም የቡድኑ አባል እንደነበሩ የእግርኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.