Fana: At a Speed of Life!

መሃመድ ሞክበር የኢራን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ መሃመድ ሞክበርን የኢራን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡

መሃመድ ሞክበር በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው ያለፉት ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ምክትል እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ አደጋ ሕይወታቸው ያለፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዱላሂን በመተካት ደግሞ አሊ ባጌሪ ካኒ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡

አሊ ባጌሪ ካኒ ቀደም ሲል የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

በኢራን ከ50 ቀናት በኋላ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚካሄድ መገለጹንም አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል፡፡

በተያያዘ ዜና በሄሊኮፕተር አደጋው ለደረሰው ሀዘን የተለያዩ ሀገራት ለኢራን ህዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል።

በዚህም የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ፣ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼሃባዝ ሻሪፍ ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የቬንዝዌላው ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማድሮ እና በርካታ የሀገራት መሪዎች ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.