Fana: At a Speed of Life!

የቻይናው ሳውዝ ዌስት ሆስፒታል ለመከላከያ ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ሳውዝ ዌስት ሚሊተሪ ሆስፒታል ለመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን  የተረከቡት የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ሸዋየ ኃይሌ ÷አሁን ላይ እንደተቋም የተጀመረው የሪፎርም ትግበራ እና የመሰረተ ልማት ስራዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

ተገንብቶ በቅርቡ ስራ የጀመረው  የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ግዙፍ እና በውስጡ በርካታ ዘመናዊ ግልጋሎቶችን የመስጠት አቅም ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሆስፒታሉን ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች  አንዱ በአይነቱ ልዩ የሆነ የላቦራቶሪ ማዕከል ያለው መሆኑ ነው ያሉት ዋና አዛዧ ÷ከቻይና ሳውዝ ዌይስት ሚሊተሪ ሆስፒታል ድጋፍ የተደረገው የህክምና ቁሳቁስ ለዚህ ግልጋሎት የሚውል ነው ብለዋል፡፡

ድጋፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ከማጠናከሩም ባሻገር በጤናው ዘርፍ የተሻለ ስራን ለመስራት ሁሉም የራሱን ድርሻ እየተወጣ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.