Fana: At a Speed of Life!

የጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ንግግሮችና መልዕክቶችን የያዘ መጽሃፍ ለንባብ በቃ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግሮችና መልዕክቶችን የያዘ እና ከ”መስከረም እስከ መስከረም” የተሰኘ መጽሃፍ ለንባብ በቅቷል፡፡

መጽሃፉ ላይ ሙያዊ ውይይት በወዳጅነት ፓርክ መካሄዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመልክቷል፡፡

በመድረኩም ተማሪዎች ከመጽሃፉ የተመረጡ ገጾችን ለውይይት መነሻ ሃሳብ እንዲሆኑ በንባብ አቅርበዋል፡፡

በተለያዩ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ተሳታፊዎችም በመጽሃፉ የተሰነዱ መልዕክቶች ላይ ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

መጽሃፉ ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከመስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ ሀገር አቀፍ ሁነቶች፣ ዓለም አቀፉ ጉባዔዎችና በዓላት ላይ ያስተላለፏቸውን 91 መልክቶችና ንግግሮች መያዙ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.