Fana: At a Speed of Life!

ለመጀመሪያው ዙር የሐጅ ተጓዦች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘንድሮው 1 ሺህ 445ኛው የሐጅ ሥነ-ሥርዓት የመጀመሪያ ዙር ተጓዦች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደረገ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራርና ሠራተኞች በተገኙበት ሽኝቱ ተደርጓል፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሼኽ ሃሚድ ሙሳ፤ በሂደቱ የምዘገባ፣ የቪዛ፣ የምክርና ተያያዥ አገልገሎቶች በተቀላጠፈ መልኩ መሰጠታቸውን ገልጸዋል።

ለሃጅ ስነ ስርአቱ ከጉዞ እስከ መመለሻ ድረስ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው አመት 11 ሺህ ሑጃጆች መጓዛቸውን አስታውሰው ዘንድሮ ደግሞ ከ12 ሺህ በላይ ተጓዦች ወደ ስፍራው የሚያቀኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በዛሬው እለት የመጀመሪያው ዙር የሁጃጆች የሽኝት ስነ ስርአት መደረጉን ተናግረዋል።

ለጉዞው መሳካት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ ባንኮችና ሌሎችም አካላት ለነበራቸው የላቀ ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

የሁጃጆች ጉዞ ለአንድ ወር የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው የተጀመረው አገልግሎትና ቀልጣፋ መስተንግዶ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.